የአርሰናል እና ብራይተን በ1-1 በተለያዩበት ጨዋታ ላይ ዲክላን ራይስን ካርድ ያሳየው ዳኛ ክሪስ ካቫናግ፣ ይህንን አከራካሪ ውሳኔውን እንዳልወደደው ነገር ግን ምርጫ እንዳልነበረው ገልጿል።
በMatch Officials Mic’d ፕሮግራም ላይ የተሰማው የክሪስ ካቫናግ ድምጽ እንዲህ ይላል፡ “ዲክ፣ መውጣት አለብህ። ህጉን አልወድም፣ አልወድም። ነገር ግን ራይስ ኳስን መትቷል። ኳሱን ምትቷል። ዲክ፣ አዝናለሁ መውጣት አለብህ።”
ይህ ዜና የእግር ኳስ ህጎች እና የዳኞች ውሳኔዎች ላይ ያለውን ውዝግብ ያሳያል። ዳኛው ራሱ በህጉ ላይ ያለውን አለመስማማት ቢገልጽም፣ ህጉን መከተል እንዳለበት ተገድዷል።